በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ላይ የሚፈጸመው እስራት እንደቀጠለ ነው ሲል ምርጫ ቦርድ ተናገረ፡፡
ምርጫ ቦርድ ይህን ያለው የ2016 በጀት ዓመት የ11 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርትን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ነው፡፡
በተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚነሱ ቅሬታዎችን እና አቤቱታዎችን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በተቻለ ፍጥነት መልስ በመስጠት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ምን ያክል ጥረት አድርገሃል የሚል ጥያቄ ምርጫ ቦርደ በቋሚ ኮሚቴዎች ተጠይቋል፡፡
ለጥያቄዉ ምላሽ የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሲታሰሩ እንዲለቀቁ ለፖሊስ እና ለክልል የጸጥታ ተቋማት ቦርዱ ደብዳቤ ይጽፋል ብለዋል፡፡
ከዚያ በላይ ከሆኔ ደግሞ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ አቤቱታ ካቀረበው እና ከምርጫ ቦርድ አድርጎ ኮሚቴ የቋቁም እና ችግሩ እንዲታይ ያደርጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ላይ የሚፈጸመው እስራት እንደቀጠለ ነው ያለው ምርጫ ቦርድ ያለኝ አቅም በተሰጠኝ ሃላፊነት መሰረት አንድ የፓርቲ አባል ሲታሰር የት እንዳለ በምን ሁኔታ እንዳለ ፍረደ ቤት መቅረብ አለመቅረቡን ለማጣራት ይህን ላደረገው አካል ደብዳቤ እጽፋለሁ ብሏል፡፡
በማገኘው ግብአትም ነው ወደ ቀጣይ እርምጃ የሚሄደው ያለው ምርጫ ቦርድ አሁን ግን ደብዳቤ በተደጋጋሚ ብጽፍም ምልሽ እያገኘሁ አይደለም ማለቱ ሲል ለምክር ቤት ሲስረዳ ሰምተናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comentarios