top of page

ሰኔ 21፣ 2016 - በመጪው የትምህርት ዘመን ፈቃዳቸው በተሰረዘባቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩት 29,000 ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ ለወላጆች ላይ ስጋት ፈጥሯል

  • sheger1021fm
  • Jun 28, 2024
  • 1 min read

በመጪው የትምህርት ዘመን ፈቃዳቸው በተሰረዘባቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩት 29,000 ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ ለወላጆች ላይ ስጋት ፈጥሯል፡፡


የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ ተማሪዎቹ በሌሎች ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ አመቻቻለሁ ብሏል፡፡


41 ትምህርት ቤቶቹ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ባለማስተማር እና በሌሎች የፖሊሲ ጥሰቶች ምክንያት ፍቃዳቸው ተሰርዟል መባሉ ይታወቃል፡፡


ቀሪዎቹ ደግሞ ፍቃዳቸውን በራሳቸው ፍላጎት የመለሱ መሆናቸው የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣኑ በሰጠው መግለጫ ተናግሮ ነበር፡፡


ባለስልጣኑ አክሎም በመጪው ዓመት አገልግሎት አይሰጡም በተባሉት ትምህርት ቤቶች ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎችን ወደ ሌሎች የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች መማር እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡


ፈቃዳቸው በተነጠቁ ትምህርት ቤቶች ሲያስተምሩ የነበሩ ወላጆች በበኩላቸው ልጆቻችንን የት ማስተማር እንዳለብን አናውቅም? ልጆቻንን ለማስተማር የሚችል በቂ ትምህርት ቤት ማግኘት አለማግኘታችን ሌላኛው ስጋታችን ነው ይላሉ፡፡


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page