top of page

ሰኔ 20 2017 - ዩኒሊቨር የቫዝሊንን ምርቶቹን በሸጥታ አምጥቶ በኢትዮጵያ ገበያ መሸጥ መጀመሩን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • Jun 27
  • 1 min read

ኩባንያው ይህንን የተነገረው በትላንትናው እለት ምርቱን ማስገባት መጀመሩን ይፋ ባደረገበት ስነስርዓት ላይ ነው።


በዝግጅቱ ላይም የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን እንዲሁም በኢትዮጵያ የብሪታንያ አምባሳደር ዳረን ተገኝተዋል።


ዩኒሊቨር ቫዝሊንን በኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ የጀመረው የውጭ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ በቀጥታ እንዲያስገቡ መፈቀዱን ተከትሎ መሆኑን አስረድቷል።

ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ነሲቡ ተመስገን "የቫዝሊን ምርትን በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ለማስመጣት ያገኘነው ዕድል፣ ለእኛ ትልቅ ለውጥ አምጪ ነው" ብለዋል፡፡


የቫዝሊን ምርት ከ150 ዓመታት በላይ ቆዳን ለመንከባከብ፣ ጤና እና ውበትን ለመጠበቅ አገልግሎት ላይ መዋሉ ተነግሯል።


ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሮውን የከፈተው ከዛሬ 11 ዓመት በፊት ሲሆን በሰኔ 2008 ኩባንያው በዱከም ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ፋብሪካውን በይፋ ማስመረቁን አስታውሷል።


ፋብሪካውም የዩኒሊቨር በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ምርቶችን እንደ ላይፍቦይ፣ ኦሞ፣ ክኖር፣ ሰንላይት እና ሲግናል በማምረት ላይ ይገኛል።


ኩባንያው በኢትዮጵያ ከ7,000 በላይ ሠራተኞችን እነደሚያሰራ፣ በየዓመቱ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ግብር እንደሚከፍልም አስረድቷል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page