top of page

ሰኔ 20፣ 2016 - የኢትዮዽያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በከተማው የተፈጠረው የነዳጅ ማደያ ላይ ሰልፍ በሁለት ቀን ይፈታል አለ

የኢትዮዽያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በከተማው የተፈጠረው የነዳጅ ማደያ ላይ ሰልፍ በሁለት ቀን ይፈታል አለ።


የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ እስመለአለም ምህረቱ አዲስ አበባ ላይ የሚታየው የነዳጅ እጥረት የአቅርቦት ሳይሆን የስርጭት ችግር ነው ሲሉ ለሸገር ነግረዋል።


በጅቡቲ ሆራይዘን ላይ ያለው ተርሚናል በባለፈው የአረፋ በአል ምክንያት ነዳጅ የመጫን ስራ ተስተጓልሏ ተብሏል።


ሁለት ቀን ነዳጅ የመጫን ስራ ባለመሰራቱ ይህ እየተንከባለለ መምጣቱን ሀላፊው ለሸገር ነግረዋል፡፡


ነዳጅ አዳይ ድርጅቱ ከሱሉልታ ቤንዚን፣ ከአዋሽ መጠባበቅያ ደግሞ ናፍታ አቅርበናል ብሏል፡፡


ችግሩም በሁለት ቀን እንደሚፈታ አቶ እስመለአለም ለሸገር ነግረዋል፡፡


የኢትዮጵያ የነዳጅ አዳዮች ማህበር በበኩሉ የነዳጅ አቅርቦት ችግር አለ ይላል፡፡


የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ለተሽከርካሪዎች በበቂ ሁኔታ ነዳጅ ማጠጣት የሚችሉ ግዙፍ ማደያዎች በመጠናቸው ልክ ነዳጅ እየቀረበላቸው ባለመሆኑ የተከሰተ ነው ሲሉ ለሸገር ነግረዋል፡፡Comments


bottom of page