top of page

ሰኔ 19፣ 2016 - ብክለትን ለመቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያዎችና ህጎች ቢኖርም ተፈጻሚ እየሆኑ አይደለም ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jun 26, 2024
  • 1 min read

ብክለትን ለመቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያዎችና ህጎች ቢኖርም ተፈጻሚ እየሆኑ አይደለም ተባለ።


በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢን የሚበክሉ ግለሰቦችና ተቋማትን ተጠያቂ የማድረጉ ስራም ትልቅ ከፍተት አለበት ተብሏል።


የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአካባቢ ህግ ተከባሪነት ዳይሬክተር፤ ለሜሳ ጉደታ የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር በአካባቢ ጥበቃ ህግ መሰረት ህጉን ተላልፈው የተገኙ አካላትን እስከ አስር ዓመት ድረስ የሚደርስ የስር ቅጣት የሚያስፈርድ የወንጀል ድርጅቶች ቢኖርም እስካሁን ግን ተፈጻሚ ሲሆኑ አይታይም ብለዋል።


በሌላ በኩል የፀጥታ አካላት እንደ ሌሎች ደረቅ ወንጀሎች በህገ-ወጥ መንገድ ፍሳሽን ወደ ወንዞች የሚያገናኙ እና በመሰል ድርጊቶች አካባቢን የሚበክሉ አካላትን እምብዛም እንደማይቆጣጠሩ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ል ስራ አስኪያጅ ዋለልኝ ደሳለኝ ነግረውናል።



תגובות


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page