top of page

ሰኔ 19፣ 2016 - በኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ከሚሰሩ የመንግስት ተቋማት መካከል በአግባቡ ስራቸውን የሚከውኑት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ተባለ

በኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ከሚሰሩ የመንግስት ተቋማት መካከል በአግባቡ ስራቸውን የሚከውኑት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡


ከመንግስት ተቋማት ይልቅ የግል ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው የሚከፍሉት ክፍያ ከፍ ማለቱ ደግሞ ባለሞያዎች ወደ ግል ድርጅቶቹ ማዘንበል ሌላኛው የውስጥ ኦዲት በሚፈለገው ልክ ውጤታማ ስራ እንዳይከወን ምክንያት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡


በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ብሄራዊ ባንክ በውስጥ ኦዲት ሙያ ከበረቱት ተቋማት መካከል መሆናቸውን ሰምተናል፡፡


በኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ዘርፍ ላይ ብዙ መስራት ይጠበቃል የተባለ ሲሆን ጥቂት ከሚባሉ ተቋማት ውጭ የውስጥ ኦዲት እንደሀገር እየተሰራበት አይደለም ተብሏል፡፡


በተለያየ ጊዜ ተቋማቱ ላይ የሚመጣ ትችት፣ የመልካም አስተዳደር እክል እና ሌሎችም በድርጅቱ ላይ የሚደርሱ ችግሮች በውስጥ ኦዲት ሙያ ላይ ያለቸው አስተዋፆ አናሳ በመሆኑ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡


የውስጥ ኦዲት በአግባቡ እንዲሰራ ተቋማት የሚያግዘው የኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ኢንስቲቲዩት ከአለም አቀፉ የውስጥ ኦዲተሮች ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ስራዎችን እንደሚከውን ይናግራል፡፡


ይሄው ኢንስቲቲዩት ተቋማቱ ለሰሩት የውስጥ ኦዲት ማረጋጫ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሚከውነው ስራም ችግሮች እንደሚያጋጥሙት የኢንስቲቲዩቱ ፕሬዚደንት ገነት ሐጎስ ተናግረዋል፡፡


ፋሲካ ሙለወርቅ



Commentaires


bottom of page