top of page

ሰኔ 19፣ 2016 - በኢትዮጵያ ከ1940ዎቹ ጀምሮ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተሰጠው የታሪክ ት/ት የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዳልቻለ ጥናት አሳየ

  • sheger1021fm
  • Jun 26, 2024
  • 1 min read

በኢትዮጵያ ከ1940ዎቹ ጀምሮ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሰጠው የታሪክ ትምህርት የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዳልቻለ ጥናት አሳየ፡፡


ጥናቱ የኢትዮጵያ የታሪክ ባለሞያዎች ማህበር እና የሰላም ሚኒስቴር ‘’ታሪክ ለሕብረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ’’ በሚል መሪ ሃሳብ በተሰናዳ መድረክ ላይ የቀረበ ነው፡፡


የታሪክ ትምህርት ለተማሪዎች ሚሰጠው፤ ከቀደመው ስህተት ለመማር እና ያለፈውን ጠንካራ ታሪኮች ደግሞ አጉልቶ ለትውልድ ማቀበል ቢሆንም ያን ማድረግ ባለመቻሉ እርስ በእርሳችን በታሪክ ድንጋይ እንድንወራወር መንስዔ ሆኗል ተብሏል፡፡


ታሪክ፤ ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ መሳርያ መሆን ሲገባው የግጭት፣ የንትርክ እና ያለመግባባት ምክኒያት ሆኗል ያሉት ጥናቱን ያቀረቡት የታሪክ መምህሩ አገሩ ሹሜ ናቸው፡፡


የታሪክ መምህሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሰጠው የታሪክ ትምህርት ውጤታማ መሆን ያልቻለበት ምክንያት ሲስረዱ ውጫዊ እና ውስጣዊ በሚል ለሁለት ከፍለዋቸዋል፡፡


የውጪ ተጽኖን ሲስረዱ የትምህርቱ ይዘት የውጪ መሆኑ ነው ይላሉ፡፡


የ1950ዎቹ የትምህርት ሥርዓቶች የውጪ ታሪኮች የሚበዙበት ነው ያሉት የታሪክ መምህሩ አገሩ ሹሜ፤ 1960 ግን በተሻለ ሁኔታ የኢትጵያን ታሪክ ለማካተት ተሞክሯል ብለዋል፡፡


በ1950 ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዲሰጥ ከተያዘው የታሪክ ትምህርት አምስት ዋና ዋና ይዘቶች የያዘ ቢሆንም የኢትዮጵያ አንድም ታሪክ አላካተተም ነበር ብለዋል፡፡


ይሁንና የአፍሪካ አንግል አንድ አጀንዳ በውስጡ የያዘ እንደነበር ተነግሯል፡፡


በአራቱም የትምህርት ሥርዓቶች የኢትዮጵያ ታሪክ ዝቅተኛ እንደሆነ ጥናት አቅራቢው አስረድተዋል፡፡


ይህም በመቶኛ ሲሰላ የኢትዮጵያ ታሪክ ዜሮ በመቶ የአፍሪካ 20 በመቶ ቀሪው 80 በመቶ የአለም ታሪክ ነው ብለዋል፡፡


ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ውጪውን እንድናስብ ያደረገ የትምህርት ሥርዓት ነው ሲሉ የታሪክ መምህሩ አስረድተዋል፡፡


Opmerkingen


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page