ለመንግስት ሆስፒታሎች ከሚቀርቡና በብዙ የውጭ ምንዛሬ የሚሸመቱ የመመርመሪያ መሳሪያዎች ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጡ ከስራ ውጭ ሲሆኑ ይታያል፡፡
ይህም መሳሪያዎቹ በቂ መለዋወጫ እንዲሁም ለስራው የሚያስፈልጉ ኬሚካሎች ያልተሟሉላቸው በመሆኑ ነው ሲሉ የጤና ተቋማቱ ይናገራሉ፡፡
ለመንግስት የጤና ተቋማት የህክምና መሳሪያዎችን የሚያቀርበው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በበኩሉ በዚህ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ግብዓቶቹን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር ለ3 ዓመታት ሳይቆራረጥ እንዲቀርብ ውል እያሰርኩ ነው ብሏል፡፡
በህክምና ግብዓት አቅርቦቱ ላይ የሪኤጀንቶች ስርጭት ያልተቆራረጠ እንዲሆን የመንግስትና የግል አጋርነት ወይም ፐብሊክ ፕራይቬት ፓርትነርሽፕ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ መታሰቡን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…
ምህረት ስዩም
Comments