ሰኔ 18 2017 - የፌዴራል የመንግስት ንብረት የሆኑ 37 ባለ አንድና ሁለት ወለል ህንፃዎችን የማይመለከተው ተቋም ኪራይ እየሰበሰበባቸው ነው ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Jun 25
- 1 min read
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የፌዴራል መንግስት የሆኑ የኪራይ ቤቶችን የማስተዳደር ስልጣን ቢኖረውም በድሬዳዋ ከተማ ያሉ 37 ህንፃዎችን እና አንድ መጋዘን ግን እያስተዳደራቸው አይደለም ተብሏል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት ባካሄው የክዋኔ ኦዲት የተጠቀሱትን ቤቶችና መጋዘኑን ከህግ ውጭ ላለፉት 20 ዓመታት አከራይቶ ኪራይ የሚሰበሰብበት የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ነው ብሏል፡፡
በሌላ በኩል የተለያዩ 10 የፌዴራል እና የአዲስ አበባ አስተዳደር ተቋማትም ለኮርፖሬሽኑ በአግባቡ ኪራይ እየከፈሉ እንዳልሆነ የኦዲት ምርመራው አረጋግጧል፡፡
በዚህም ኮርፖሬሽኑ ከ29 ሚሊየን ብር በላይ ሳይሰበሰብ ቀርቷል ተብሏል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከ2,700 በላይ የቤት ይሰጠን የጥያቄዎችም ቀርበውለት ምላሽ ያልሰጠ መሆኑ በኦዲት ግኝት ተካትቷል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments