top of page

ሰኔ 18 2017 - በ2017 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍልከተፈተኑ 168 የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ውስጥ 151ዱ ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን መሸጋገራቸውን ቢሮው በመግለጫው ተናግሯል

  • sheger1021fm
  • Jun 25
  • 1 min read

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ከ70,000 በላይ ተማሪዎች ከ62,000 በላይ ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን አልፈዋል ተባለ።


በከተማዋ ያሉ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 3 እና 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከተማ አቀፍ ፈተና መውሰዳቸው ይታወሳል።


በዚህ ካስፈተንኳቸው 70,525 ተማሪዎች መካከል 62,639 ወይም 89 በመቶዎቹ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ በመሆናቸው ወደ ቀጣዩ የትምህርት ክፍል ተሸጋግረዋል ብሏል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ።


በዚህም 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል ይሻገራሉ የተባለ ሲሆን የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ 45 በመቶ እና ከዚያ በላይ ካመጡ ወደ ቀጣዩ የትምህርት ክፍል ይሻገራሉ፡፡


በ2017 የትምህርት ዘመን ከተፈተኑ 168 የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ውስጥ 151ዱ ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን መሸጋገራቸውን ቢሮው በመግለጫው ተናግሯል።


656 ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸው የተነገረ ሲሆን 276 ትምህርት ቤቶች 100 በመቶ ያሳለፉ መሆናቸውን ሰምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page