top of page

ሰኔ 18 2017 - በአዲስ አበባ የነዳጅ ምርት በመደበቅ እጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል የተባሉ 3 የነዳጅ ማደያዎች ታሽገዋል፤ ሰራተኞቹም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ

  • Jun 26, 2025
  • 1 min read

በአዲስ አበባ የነዳጅ ምርት በመደበቅ እጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል የተባሉ 3 የነዳጅ ማደያዎች ታሽገዋል፤ ሰራተኞቹም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡


በከተማዋ በቂ የነዳጅ አቅርቦት አለም ተብሏል፡፡


በአዲስ አበባ የሚከወነውን የነዳጅ ግብይት የሚቆጣጠረውን የከተማዋን ንግድ ቢሮ ከሰሞኑ በከተማዋ የሚስተዋለው ረጃጅም የነዳጅ ሰልፍ ከምን የመጣ ነው ስንል ጠይቀነዋል፡፡


የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አሸናፊ ብርሃኑ እርግጥ ነው ከሰሞኑ ባደረግነው ክትትል ናፍጣ ለመቅዳት የሚደረጉ ረጃጅም ሰልፎች ነበሩ ይህ የተፈጠረው እጥረት ኖሮ ሳይሆን ጥቂት ማደያዎች ዋጋ ሊጨምር ይችላል በሚል የነዳጅ ምርት በመደበቅ እጥረት እንዲፈጠር በማድረጋቸው ነው ብለዋል፡፡

በተለይም ባለፉት የቅዳሜና እሁድ ቀናት በርከት ያለ መጠን ያለው የነዳጅ ምርት ሸሽገው ተገኝተዋል የተባሉት ማደያዎች ተዘግተዋል ባለቤቶቹና ሰራተኞቹ በቁጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ያሉን ሃላፊው የትኞቹ ማደያዎች እንደሆኑም በዝርዝር አስረድተዋል፡፡


በከተማዋ ያሉ 125 ማደያዎች ምን ያህል ነዳጅ ይዘዋል፤ግብይቱንስ እንዴት እየከወኑት ነው የሚለውን በቀን በቀን 3 ጊዜ እንደሚቆጣጠሩ የነገሩን አቶ አሸናፊ በአሁኑ ወቅት ከተማዋ የሚያስፈልጋት ያህል የነዳጅ ምርት አለ፤የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየውም ከ6 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ አለ፤በሁሉም ማደያዎች የነበሩት ሰልፎች እየቀነሱ ግብይቱ የተረጋጋ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ነዳጅ የሚጭኑ ቦቴዎችን በተመለከተ የተቀመጠው ስታንዳርድ እደሚያሳየው ነዳጅ የጫነ ቦቴ ከጂቡቲ ተነስቶ በ3 ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ መድረስ ይኖርበታል፡፡


ይሁንና የተለያዩ ምክንያችን በመጥቀስ መንገድ ላይ ሆን ብለው የሚዘገዩ ቦቴዎችም ሰው ሰራሽ እጥረት እየፈጠሩ ነው፤  በዚህ በኩል በተሰራው የቁጥጥር ስራ ባለፈው እሁድ ብቻ መንገድ ላይ የቆዩ 16 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ አዲስ አበባ ገብተው እንዲያራግፉ በመደረጉ የነበረው እጥረት ተቀርፏል ብለውናል፡፡


በንግድ አዋጁ መሰረት ምርቶችን የመደበቅ ወንጀል ከ300,000 እስከ 500,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና የማደያ ባለቤቱን ከ2 ዓመት እስከ 3 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እንደሚያስቀጣ  መሆኑም ተጠቁሟል፡፡


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም  ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የሃዲዱ ጠባቂ የፀጥታ አካላት የተዘጋውን መወጣጫ(ራምፕ) እንዲከፍቱላቸው ቢጠይቁም የተሰጣቸው ምላሽ እስከ ድብደባ የደረሰ

 
 
 
የነሐሴ 7 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ ከአውሮፓ የሚባረሩ የ3ኛ አገር ስደተኞችን ልትቀበል ነው ተባለ፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ተቀብላ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን ካቲሜሪኒ የተሰኘ የግሪክ ጋዜጣ መዘገቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ጋዜጣው ዘገባውን ያሰራጨው ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን በዋቢነት በመጥቀስ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሐሳቡ ቀዳሚ አፍላቂዎች

 
 
 

1 Comment


Vansh Sharma
Vansh Sharma
Jun 26, 2025

If you want an experience that can be described as mind-blowing, contact the Escorts in Aerocity! Our hot beautifulness is trained to deliver the best companionship, and the best intimate experiences!

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page