top of page

ሰኔ 18፣ 2016 - የኢትዮጵያ ቱሪዝም በጦርነትና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እየተንገዳገደ መሆኑን ባለሞያዎቹ ይናገራሉ

የኢትዮጵያ ቱሪዝም በጦርነትና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እየተንገዳገደ መሆኑን ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡


እንደ አውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄዱ የሚከለክል የጉዞ ክልከላ መረጃዎች ሲያወጡ ነበር፡፡


በዚህም ምክንያት ከውጪ ሀገራት የሚመጡ ቱሪስቶች እየቀነሱ መሆኑን ይሰማል፡፡


ወርልድ ኢኮኖሚ ፎረም ግንቦት ወር ላይ በ2024 ተወዳዳሪ የቱሪስት መዳረሻ ናቸው ብሎ 119 ሀገራትን ይፋ ባደረገበት መረጃው ኢትዮጵያን ሳያካትታት አልፏል፡፡


ተቋሙ በየዓመቱ ተመሳሳይ መረጃዎችም ያወጣል፡፡



Comments


bottom of page