ሰኔ 18፣ 2016 - ቤት የሚያከራዩ የውጭ ሀገር ዜጎች የተቀመጠውን መመሪያ እንዲከተሉ፤ ከተማው አሳስቧል
- sheger1021fm
- Jun 25, 2024
- 1 min read
ቤት የሚያከራዩ የውጭ ሀገር ዜጎች የተቀመጠውን መመሪያ እንዲከተሉ፤ የከተማው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አሳስቧል፡፡
ቢሮው በአዲስ አበባ ከአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ጋር በተያያዘ፤ ተከራዮች የሚገጥማችሁን ማንኛውም ችግር ጠቁሙኝ ብሏል፡፡
እተከናወነ ባለው የአከራይ ተከራይ የውል ምዝገባ ቤት የሚያከራዩ የውጭ ሃገር ዜጎች ውሉን በአማርኛ ቋንቋ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ተነገሯል፡፡
በተጨማሪም ለቤቱ ኪራይ በባንክ የሚቀበሉት የኪራይ ገንዘብ በኢትዮጵያ ብር መሆን እንዳለበት የቤቶች ልማትና አስተዳደር ምክትል የቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉነህ ካሳ ተናግረዋል፡፡
ከቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ የሚኖርን ማንኛውም ቅሬታ ተቀብሎ የሚያስተናግድ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መኖሩም ተነግሯል፡፡
ከአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ምዝገባ መጀመሩን ተከትሎ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮቻቸው ላይ ዋጋ እየጨመሩ አንዲሁም ከቤት ለማስወጣትም እየሞከሩ እንደሆነ ጥቆማ ደርሶናል ያሉት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ናቸው።
ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የተጀመረው የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ እስከ ሰኔ 30 እንደሚቀጥል ይታወቃል፡፡
ምንታምር ፀጋው
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments