ኢትዮጵያ ውስጥ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ከተሰማሩት በአለም አቀፍ ደረጃ የተከለከሉ ፀረ ተባይ መድኃኒቶችን የሚጠቀሙ እንዳሉ ተነግሯል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ እና አካባቢ ብክለት ምርምር ትምህርት ክፍል በቅርቡ ባደረገው ጥናት ይህንኑ አረጋግጫለሁ ብሏል።
እንደ ዝዋይ፤ ሃዋሣ እና አርባ ምንጭ ያሉ አካባቢዎችን በሚያካልለው ‘’የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ’’እየለሙ ባሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶቹ ላይ የተካሄደው ይኸው ጥናት ፀረ ተባይ መድሃኒቶቹ እና ኬሚካሎቹ በኮንትሮባንድ እንደሚገቡ ያመለክታል።
የጥናት ቡድኑ መሪ ዶክተር ዳንኤል ወ/ሚካኤል በአለም አቀፍ ደረጃ ሲከለከሉ እንዲወገዱ ባለመደረጋቸው አሁም ድረስ ከክምችት እየወጡ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው ብለዋል።
コメント