ኢትዮጵያን እንደ ታይላንድና ህንድ የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራሁ ነው ሲል ላንሴት የህክምና ማዕከል ተናገረ፡፡
ማዕከሉ በዚህ ዓመት ከ16,000 በላይ ለሆኑ ታካሚዎች ቀዶ ህክምና አድርጌያሁ ብሏል፡፡
ኢትዮጵያዊያን በየዓመቱ ብዙ ሚልየን የሚባል የውጭ ሀገራት ምንዛሬን በማውጣት ወደ ውጭ ሀገር ለህክምና እንደሚጓዙ ይታወቃል፡፡
አሁን ግን የህክምና ባለሞያዎችን እንዳይሰደዱ እና የሀገሬ ሰዎችም ለተሻለ ህክምና ወደ ውጭ ሀገር እንዳይከራተቱ የበኩሌን እያገዝኩ ነው ይላል ላንሴት የህክምና ማእከል፡፡
ይህን በማድረጌም በአንድ ዓመት ውስጥ 16 ሺህ ታካሚዎችን በማየት፤ ለ400ዎቹ የቀዶ ጥገና በማድረግ ወደ ውጭ ከመሄድ ማስቀረቱን እና 1200ዎቹ ደግሞ ቀላል የቀዶ ህክምና ማከናወኑን ተናግሯል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments