top of page

ሰኔ 18፣ 2016 - ለፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግንባታ ከ2017 በጀት ረቂቅ ላይ 5.2 ቢሊዮን ብር ተመድቧል ተባለ

ለፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግንባታ ከ2017 በጀት ረቂቅ ላይ 5.2 ቢሊዮን ብር ተመድቧል ተባለ፡፡


የግንባታ ፕሮጀክቱ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በኩል እንደሚከወንም ተነግሯል፡፡


መንግስት፤ ለፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የቢሮ ኪራይ የሚያወጣው ገንዘብ ከፍተኛ እንደሆነና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንም ተናግሯል፡፡


ከ2017 ረቂት በጀት ላይ 5.2 ቢሊዮን ብር ተመድቦ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ለመገንባት የታሰበው፤ የፌደራል መስሪያ ቤቶች አገልግሎታቸው በተመቻቸ ሁኔታ መስጠት እንዲችሉ ነውም ተብሏል፡፡


መንግስት በየ ዓመቱ ለመስሪያ ቤቶች የቢሮ ኪራይ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚያወጣ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


መንግስትም ይህ ፕሮጀክት ለቢሮ ኪራይ የማወጣውን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ለማዳን ይረዳኛልም ብሏል፡፡


ይህ የተነገረው የገንዘብ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች የ2017 ዓ.ም ረቂቅ በጀትን በተመለከተ፤ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡


ያሬድ እንዳሻው



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page