ሰኔ 17 2017 - የ7 ዓመት ታዳጊ በመኖሪያ ጊቢ ውስጥ ባለ የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከር ውስጥ ወድቆ ሕይወቱ አለፈ
- sheger1021fm
- Jun 24
- 1 min read
ትናንት ከሰዓት በኋላ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የ7 ዓመት ታዳጊ በመኖሪያ ጊቢ ውስጥ ባለ የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከር ውስጥ ወድቆ ሕይወቱ አለፈ፡፡
ከአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንደሰማነው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ተከማ ወረዳ 14 ጋርመንት አካባቢ ነው ታዳጊው በመኖሪያ ጊቢ በነበረ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ውስጥ ወድቆ የሞተው፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያው አቶ ንጋቱ ማሞ እንደነገሩን በመኖሪያ ጊቢ የሚገኙ የፍሳሽ ማጠራቀሚያዎች ክዳን ካልተበጀላቸው አደጋው የከፋ ስለሚሆን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
ከዚህ በፊትም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መስቀል ፍላወር አካባቢ በመኖሪያ አፓርታማ ቅጥር ግቢ እንደዚሁም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ ባለ ኮንዶሚኒየም ጊቢ ውስጥ ክዳንና መከላከያ ባልተደረገላቸው የፍሳሽ ማጠራቀሚዎች ውስጥ ሁለት ታዳጊዎች ወድቀው ህይወታቸው አልፏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il












Comments