ሰኔ 17 2017 - የኢንጂነር አልቤርቶ ቫርኔሮ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በጣሊያን ሀገር ተፈፀመ
- sheger1021fm
- Jun 24
- 1 min read
ለአዲስ አበባ ምልክት የሆኑ ህንፃዎችን በማነፅ የሚታወቁት ኢንጂነር አልቤርቶ ቫርኔሮ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በጣሊያን ሀገር ተፈፀመ።
ለኢንጂነር ቫርኔሮ ዛሬ በአዲስ አበባ ለገሃር አካበቢ በሚገኘው መድሃኒአለም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የስንብት ፕሮግራም በቫርኔሮ ኮንስትራክሽን ሰራተኞች ተደርጎላቸዋል።

ኢንጂነር ቫርኔሮ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ነበሩ።
የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል ካነጿቸው መካከል ይጉኙበታል።
በቅርቡም የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሰርተዋል።
ባለፈው ሳምንት አርብ የህልፈታቸው ወሬ የተሰማው ኢንጂነር ቫርኔሮ በዛሬው እለት ቀብራቸው መፈፀሙን ሰምተናል።
Comments