top of page

ሰኔ 17፣ 2016 - የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገራዊ ምክክር ከፈረሱት ሀገራት ተርታ እንዳንሆን እፈልጋለሁ አለ

  • sheger1021fm
  • Jun 24, 2024
  • 1 min read

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገራዊ ምክክር ከፈረሱት ሀገራት ተርታ እንዳንሆን እፈልጋለሁ አለ፡፡


የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሙሉጌታ አበበ በምክክሩ ከዳኑ ሀገራት ተርታ እንጂ ከፈረሱ ሀገራት ምድብ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን ብለዋል፡፡


በምክክር የዳኑ ሀገራት እንዳሉ ሁሉ የፈረሱም ሰላሉ እሱ ያሰጋናል ያለው ምክር ቤቱ አንድ ሀገር ስለሆነ ያለን ችግር ፈቺ ምክክር ማድረግ ይጠበቃል ሲል ተናግሯል፡፡


በምክክር ከዳኑ እና ከተሻገሩ ሀገራት እንጂ መግባባት ለመፍጠር በተደረጉ ምክክሮች ከተበተኑ ሀገራት ተርታ እንደንሆን መስራት አለብን ሲሉ ሰብሳቢው ሙሉጌታ አበበ ነግረውናል፡፡


በስልጣን ላይ ያሉትም ሆነ ተፎካካሪዎች ያለችን አንድ ሀገር ነው እንጂ ሌላ ሀገር የለንም ያሉት አቶ ሙሉጌታ ሁላችንም የአንድ እናት ልጆች ነን ተቀያሪ ሀገር ስለሌለን በምክክር ከዳኑ ሀገሮች ተርታ እንድንሆን የጋራ ምክር ቤቱ ይፈልጋል ብለዋል፡፡


ለዚህም ደግሞ በምክክር ከዳኑ እና ከተሻገሩ ሀገራት ደግ ደግ ተሞክሮ መውሰድ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

ምክክሩ ስር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ እንደሚፈልግ ተናግሮ ለዚህም ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አለበት ሲል የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተናግሯል፡፡


የጋራ ምክር ቤቱ 16 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘ ነው፡፡


ከነዚህ ውስጥም ስለ ምክክሩ በ14 ፓርቲዎች መካከል የጋራ መግባባት መኖሩን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሙሉጌታ ነግረውናል፡፡



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page