top of page

ሰኔ 16 2017 - ከማደርጋቸው የንግድ ድርድሮች ሁሉ ከባድ የሆነብኝ ድርድር የጠረፍ ንግድ ድርድር ነው ሲል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

  • sheger1021fm
  • Jun 23
  • 1 min read

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከአለም ንግድ ድርጅት፣ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ላይ እንደራደራለን ከባድ የሆነብን ድርድር ግን የጠረፍ ንግድ ድርድር ነው ብለዋል፡፡


ምክንያቱ ደግሞ ከኋላው የሚገፋው አካል ስላለ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡


በሌላ በኩል የሞያሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት ከኬንያ ጋር ለመተግበር በተፈጸመው ውል ላይ የቀረበውን ቅሬታ ሚኒስቴሩ እንደማይቀበለው ተናግረዋል፡፡


የሞያሌ የንግድ ምክር ቤት የስምምነቱ ነፃ የንግድ ቀጠና ስፋቱ፣ በኬንያ በኩል 100 ኪሎ ሜትር መሆኑን መናገሩ ይታወሳል፡፡


በኢትዮጵያ በኩል ግን 50 ኪሎ ሜትር ብቻ መሆኑ ተገቢ እንዳልሆነ የተናገረው ምክር ቤቱ ምክንያቱም አርብቶ አደር የሆነው የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ አይሆንም ፤ በ50 ኪ.ሜ. ርቀት ውስጥ ያሉት ከተሞችም ጥቂት ስለሆኑ፣ ቢያንስ ከድንበር እስከ 300 ኪ.ሜ ይሁንልን የሚል ጥያቄ ምክር ቤቱ መጠየቁን የተናገሩት ሚኒስትሩ ይህ የማይሆን ነው ብለዋል፡፡


ያን ያህል ርቀት ክፍት አደረግን ማለት በወጪ ንግድ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሣድራል ማለት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page