ሰኔ 16 2017 - በኢትዮጵያ ሴቶች በዘመናዊ መንገድ ለወር አበባ መቀበያ የተሰናዳውን ሞዴስ የሚጠቀሙት 30 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ጥናት አሳየ፡፡
- sheger1021fm
- Jun 23
- 1 min read
የወር አበባ መቀበያ ሞዴስ ባለማግኘታቸው ምክንያት ሴት ተማሪዎች በዓመት እስከ 40 ቀን ያህል ከትምህርት ገበታቸው እንደሚቀሩም ተነግሯል፡፡
በዚህም ምክንያት ትምህርታቸውን ከናካቴው የሚያቋርጡም እንዳሉ የተነገረ ሲሆን ችግሩ ደግሞ በተለይ በገጠር አካባቢ የከፋ መሆኑን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡
በከተሞች ላይ ቢሆንም የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ዋጋው ከ70 እስከ 200 ብር በላይ መሸጡ እና የማህበረሰቡን ኑሮ ያላማከለ በመሆኑ ሴቶች ሲቸገሩ፣ ከትምህርት ገበታቸው ሲስተጓጎሉ እና ሌሎች ችግሮች ሲደርሱባቸው እናያለን።
ከ10 ሴቶች ውስጥ አንዱ በወር አበባ ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ የምትቀር መሆኑ የተነገረ ሲሆን 62.4 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ደግሞ በወር አበባ ወቅት አሮጌ ጨርቅ የሚጠቀሙ ናቸው መባሉን ሰምተናል፡፡
በወር አበባ ወቅት ሴቶች በሚጠቀሟቸው ጤንነቱ ያልተጠበቀ ምርት ለከፋ የጤና እክል የሚዳረጉም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም ተብሏል፡፡
ለኢንፌክሽን እና መሰል የጤና ችግሮች እየተጋለጡ መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ይህንን ችግር ተመልክቻለሁ ያለው መንግስትም የሴቶች ንፅህና መጠበቂያን ከዓመታት በፊት 30 በመቶ የነበረውን ወደ 10 በመቶ እንዲሆን መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡
ነገር ግን ይህ ውሳኔ ከተሰማ ከዓመታት በኋላም በመሸጫ ሱቆች ላይ ምርቶቹ ዋጋቸው ቀንሰው ሳይሆን በብዙ ጨምሮ እንደሚታይ ታዝበናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments