ሰኔ 15፣ 2016 - የህዝብ ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገርላቸው የታጠቁ ሀይሎች የማይሳተፉበት ሀገራዊ ምክክር ይሳካ ይሆን?
- sheger1021fm
- Jun 22, 2024
- 1 min read
የእርስ በእርስ ግጭት እና አለመግባባት አዙሪት ውሰጥ ያለችው ኢትዮጵያ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር የምክክር ኮሚሽን ካቋቋመች ሁለት ዓመት አልፏታል፡፡
የተቋቋመው ኮሚሽንም የመጀመሪያ ዙር ምክክር በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡
ኮሚሽኑ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ እጀምራለሁ ብሏል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው ቅድሚያ ለምክክር ምቹ የሆነ ሁኔታ ካልተፈጠረ ምክክሩ ከግቡ እንደማይደርስ ይናገራሉ፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ኮሚሽኑን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸው ምን እንደሆነ ጠይቀናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
ተያያዥ ዘገባዎችን ለማድመጥ እነዚህ ማስፈንጠሪያዎችን ይጫኑ
Comments