የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሙሉ ከ2 ሳምንት በኋላ ዲጂታል መታወቂያ በእጃቸው ሊኖር ይገባል ተብሏል፡፡
የቀድሞዉን የወረቀት መታወቂያ በዲጂታል በመቀየሩ ስራ፤ ከ2 ሚልየን በላይ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
ቀሪዎቹ በሁለት ሳምንት ውስጥ መታወቂያቸውን ዲጂታል እንዲያደርጉት ይጠበቃልም ተብሏል፡፡
ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል መዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም አሻራ ያልሰጡ ከ5 መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች፤ ለዲጂታል መታወቂያ በአዲስ መልክ እንደተመዘገቡም ተነግሯል፡፡
የዲጂታል መታወቂያ የያዘ ሰው ቁጥር 1.7 ሚልየን እንደደረሰ ሰምተናል፡፡
ይህ የሚያሳየው ደግሞ የወረቁትን መታወቂያ የምይዘው ሰው ቁጥር በእጅጉ መቀነሱን ነው ሲል ኤጀንሲው አስረድቷል፡፡
አዲስ መታወቂያ የሚያወጡ ሰዎች የወረቁቱን መታወቂያ እንደማይሰጣቸው ተነግሯል፡፡
ታመው በአልጋ ላይ ያሉ፣ በእድሜ የገፉ ሰዎች እና በተለያዩ ጉዳዮች ዲጅታሉን መታወቅያ የማይወስዱ እስከ መጪው ታህሳስ ወር ድረስ የወረቁቱን መታወቂያ እንደሚሰጣቸው ኤጀንሲው ተናግሯል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments