ከዚህ ቀደም በዶላር የነበረውን የመሬት እና ማምረቻ ሼድ የክፍያ አሰራርን በመቀየር የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በብር እንዲከፍሉ ሊደረግ ነው።
ክፍያው በዶላር መሆኑ ቀርቶ በብር የሚሆነው የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሻሻል ነው ተብሏል።
ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው መረጃ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ ከ10 በመቶ እንደማይበልጥ ተነግሯል።
አሁን ላይ ግን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሚገኙ ኢንቨስተሮች ውስጥ 55 በመቶው የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።
በቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በተዘጋጀ የመስክ ጉብኝት ላይ ተገኝተን ዛሬ መረጃው ሲነገር ሠምተናል።
ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ወደ ኢንቨስትመንቱ እንዲመጡ ለማበረታታት መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛልም ተብሏል።
የተደረጉ የአሰራር ማሻሻያዎች ከእነዚህ መካከል እንደሆኑ ነው የተነገረው።
የታሪፍ ማሻሻያ ለማያሳየነት ተጠቅሷል።
ፍቅሩ አምባቸው
Comments