top of page

ሰኔ 13፣ 2016 - በመላው ሀገሪቱ በመጪዎቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ ተነገረ

በመላው ሀገሪቱ በመጪዎቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡


ለዝናብ መፈጠር ምክንያት የሚሆኑ የደመና ክምችቶች በመኖራቸው አዲስ አበባን ጨምሮ በመካከለኛና በምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ከበድ ያለ ዝናብ ይጠበቃል ተብሏል፡፡


በአማራ፣ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአብዛኛው ኦሮሚያ፣ በደቡብ ምዕራብና በምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡


ከባድ ዝናብ ይኖራል የተባለባቸውን አካባቢዎችም የነገሩ በኢንስቲትዩቱ በኤጀንሲው የሚቲዎሮሎጂ ትንቤና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር አሳምነው ተሾመ ናቸው፡፡


ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በብዙ የሃገራችን አካባቢዎች እየጣለ ያለውና ክረምቱ መጣሁ መጣሁ ማለቱን እያሳየ ያለው ዝናብ ክረምቱን ለሚያመርቱ አካባቢዎች የተመቸ ነውም ብለዋል፡፡


ከባድ ዝናብ ይኖራል በተባሉ አካባቢዎች ያላችሁ ጎርፍ ሊከተል ስለሚችል ጠንቀቅ በሉ ተብላቹሀል፡፡


ምንታምር ፀጋው

留言


bottom of page