top of page

ሰኔ 12 2017 - ኢትዮጵያ ከመጪው ሐምሌ ወር ጀምሮ በይፋ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መገበያየት ትጀምራለች ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jun 19
  • 1 min read

በንግድ ቀጠናው አትዮጵያ በየትኛው ሀገራት ላይ ምን አይነት ንግድ ትነግድ የሚለውን ዝርዝር ነገር የያዘው ስትራቴጂም ነገ ይጸድቃል ተብሏል፡፡


ይህን ያሉት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎነፌ(ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በፓርላማ ቀርበው የመስሪያ ቤታቸውን የ11 ወራት የስራ ክንውናቸውን ለህዝብ እንደራሴዎች ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡


ሚኒስትሩ ከሃምሌ አንድ ጀምሮ በነጻ ንግድ መገበያየት እንደሚጀመር ተናግረው ንግድ የሚጀምረውም በመጀመርያው ታሪፍ ላይ 90 በመቶ ወይንም ዜሮ ታሪፍ ባደርግናቸወ ምርቶች ላይ ነው ብለዋል፡፡


የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትረሩ አቶ ካሳሁን ጎንፌ ነገ የትግበራው ስትራቴጂ አንደሚጸድቅ ተናግረዋል፡፡

በ 2017 በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ በታሪኳ አግኝታ የማታውቀውን 7.2 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የተናገሩት ካሳሁን ጎነፌ (ዶ/ር) የበጀት ዓመቱ ሲጠናቅቅ የሀገሪቱ ዓመታዊ ወጪ ንገድ ገቢ 8 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡


በ2017 በጀት ዓመት በአስራ አንድ ወራት ከጠቅላላው የወጪ ንግድ ገቢ 4.59 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 7.21 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል ብለዋል፡፡


ይህም ከ2016 በጀት ዓመት ከተገኘው 3.26 ቢሊዮን ጋር ሲነፃፀር የ3.96 ቢሊዮን ዶላር (121.48 ከመቶ) ጭማሪ አሳይቷል ሲሉ አስረድተዋል።


ለገቢው መገኘት የግብርና ምርቶች 118.44 ከመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 57.37 ከመቶ፣ ማዕድን ዘርፍ 425.16 ከመቶ ሲሆን ኤሌክትሪክና ሌሎች ምርቶች 115.91 ከመቶ ዕቅድ አፈፃፀም አሳክተዋል ተብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page