top of page

ሰኔ 12 2017 - በህጋዊም ሆነ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አረብ ሀገራት እና ሌሎችም ሀገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም

  • sheger1021fm
  • Jun 19
  • 1 min read

ያልፍልኛል ነገዬ የተሻለ ይሆናል ብለው በህጋዊም ሆነ በህገ ወጥ መንገድ ባህር ተሻግረው ወደ አረብ ሀገራት እና ሌሎችም ሀገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡


በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡት ኢትዮጵያውያን ቀን ሌት ሳይሉ ተጉዘው፣ ባህር አቋርጠው እድል ከቀናቸው ያሰቡበት ቦታ ይደርሳሉ፡፡


እዚያ ከደረሱ በኋላም ግን ሁሉም ነገር እንዳሰቡት ሳይሆንላቸው ይቀርና ብዙ ፈተናዎችን ይጋፈጣሉ፡፡


ገሚሱ ሰውነቱ ላይ ጣል ያደረገውን ጨርቅ ብቻ ይዞ ባዶ እጁን ወደ ሀገሩ ይመለሳል፣ ገሚሱ ህይወቱን ያጣል፣ ከፊሉ ደግሞ የጤና መታወክ ያጋጥማቸው እና ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡

ree

በህጋዊ የሚሄዱትም ቢሆን እንደዚህ ዓይነት ችግሮች ሲያጋጥማቸው ማየት አልያም ደግሞ ረጅም ዓመታትን ሰርተው ምንም ዓይነት አንጡራ ሀብት ሳይኖራቸው ይመለሳሉ፡፡


መንግስትም ከስደት ተመላሽ ሰዎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በሚያጋጥሟቸው ችግሮች ተመልሰው ለስደት እንዳይዳረጉ የስራ እድልን እየፈጠርኩላቸው ነው ሲልም ይሰማል፡፡


በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ የስራ እና ክህሎት ቢሮ በተሰጠኝ ሀላፊነት መሰረት ከስደት ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሰዎች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው እያደረኩ ነው ብሏል፡፡


ከስደት ተመላሾች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ከማድረግ ባለፈ የተሰዳጅ ቁጥርን እንዲቀንስ እየሰራሁ ነው ያለው ቢሮው ለዚህም በመደበኛ ፕሮግራም የስራ እድሎችን እያመቻቸ መሆኑን ተናግሯል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page