top of page

ሰኔ 12፣ 2016 - የማዕድን ሚኒስቴር፤ ከ2010 እስከ 2016 የመጀመሪያ ሩብ አመት 4.2 ቢሊዮን ዶላር  ለመሰብሰብ አቅዶ መስብሰብ የቻለዉ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነዉ ተባለ

የማዕድን ሚኒስቴር፤ ከ2010 እስከ 2016 የመጀመሪያ ሩብ አመት 4.2 ቢሊዮን ዶላር  ለመሰብሰብ አቅዶ መስብሰብ የቻለዉ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነዉ ተባለ፡፡

 

ማዕድን ሚኒስቴር ከተቋቋመ ከ50 ዓመት በላይ ቢሆንም፤ የማዕድን ሃብትና ልማትን የሚመለከት ፖሊሲ ሪፖርቱ እስከተጠናከረበት ድረስ አዘጋጅቶ ተግባራዊ አላደረገም መባሉ ተነግሯል፡፡

 

ይህም የእቅዱን 28.9 በመቶ ብቻ ሲሆን ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የነበረባትን የዉጭ ምንዛሪ እንዳታገኝ አድርጓታል ሲል የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ተናግሯል፡፡

 

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2015 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ሲቀርብ ነዉ ይህን ያለዉ፡፡

 

መስሪያ ቤቱ፤ የማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ኢንዱስትሪ ግብዓቶችን እና ዉጤቶችን በሀገር ውስጥ  ለመተካት የድንጋይ ከሰል ለማምረት እና ያመረቱትን ፐሮሰስ ለማድረግ ፍቃድ የሰጣቸዉ 9 ኩባኒያዎችን ወደ ስራ እንዳልገቡ አረጋግጫለዉ ብሏል፡፡

 

በባህላዊ መንገድ ወርቅ በሚመረትባቸዉ 36 ቦታዎች፤ የወርቅ ማጠብያ ማሽን በማዘጋጀት ማዕድኑ ለሚገኝባቸዉ ክልሎች የተሰራጨ እና ስልጠና የተሰጠ ቢሆንም ማሽኖቹ ስራ ላይ ስለመዋላቸዉ  ክትትል እንዳላደረግም በሪፖርቱ ተነግሯል፡፡

 

ከ2013 እስከ 2016 ለብሄራዊ ባንክ የሚቀርበዉ ወርቅም በመጠን ከዓመት ዓመት እየወረደ ነዉ  ተብሏል፡፡

 

ያሬድ እንዳሻው

 

Comments


bottom of page