ሰኔ 12፣ 2016 - ''የመሬት አቅርቦት ጥያቄን ጨምሮ በአበባና አትክልት ልማት ለተሰማሩ ምላሽ ለመስጠት መንግስት በትኩረት ይሰራል'' ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሣ ተናገሩ
- sheger1021fm
- Jun 19, 2024
- 1 min read
የመሬት አቅርቦት ጥያቄን ጨምሮ በአበባና አትክልት ልማት ለተሰማሩ ባለሃብቶች ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት መንግስት በትኩረት ይሰራል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሣ ተናገሩ።
ዘርፉ በትንሽ ድጋፍ የተሻለ ገቢ እያስገኘ ነው ሲሉም ሚኒስትር ድኤታዋ ትናንት ቆቃ እና ቢሾፍቱ በሚገኙ የአበባ እርሻዎች በነበረ የመስክ ጉብኝት ላይ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከሃያ አመት በፊት ከአበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ስራስር እና መዓዛማ ምርቶች ታገኝ የነበረው ወደ 24 ሚሊየን ዶላር ነው።
አሁን ላይ ግን ከዚህ ዘርፍ በያመቱ የሚገኘው ገቢ ከግማሽ ቢሊየን ዶላር መሻገሩን፣ የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ስራ ስር እና መዓዛማ ውጤቶች አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለዘርፉ ካላት እምቅ አቅም አኳያ ግን የሚገኘው ገቢ አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ነው የሚባል እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።
Comments