ሰኔ 12፣ 2016 - ከፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የክዋኔ ኦዲት አፈጻጻም እና ዋና ዋና ግኝቶች ሪፖርት መካከል በጥቂቱ
- sheger1021fm
- Jun 19, 2024
- 2 min read
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
• ለመኪና ኪራይ ከገባዉ ዉል ዉጭ 3.9 ሚሊዮን ብር የአላግባብ ክፍያ ፈጽሞ ተገኝቷል፡፡
• የገባቸዉን የፕሮጀክቶች ዉሎች በእቅዱ መሰረት ባለማስፈጸሙ መንግስትን ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አስወጥቷል፡፡
• የዳታ ማዕከልን ማሻሻል ፕሮጀክትን በወቅቱ ባለማጠናቀቁ መንግስትን ተጨማሪ ከ277 ሚሊዮን ብር በላይ አስወጥቷል፡፡
• በዲጂታል ትራንስፎረሜሽን ፐሮጀክት ላይ የቅጥር ውል ሳይኖራቸዉ እና ዉላቸዉ ለተቋረጠ ሰራተኞች የስራ ግብር እና ጡረታ ተቀናንሶ ኣለአግባብ 2.98 ሚሊዮን ብር ደመወዝ ከፍሏል፡፡
• በዲጂታል ትራንስፎረሜሽን ፐሮጀክት ላይ የተቀጠሩ ጊዜያዊ ሰራተኞች የቅጥር ዉላቸዉ ሲቋረጥ 8.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት እንዳልመለሱ ተነግሯል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
• ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2014 ዓ.ም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክኒያት ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸዉ ሴቶች የሚዉል 71.14ሚሊዮን ብር አስመድቦ የነበረ ቢሆንም ጥቅም ላይ ያዋለዉ 25.96 ሚሊዮን ነዉ፤ ቀሪዉን 45.17 ሚሊዮን ብርን አግልግሎት ላይ እዳልዋለ ማረጋገጡን የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ተናግሯል፡፡
ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
• የፓስፖርት አሰጣጥ ውጤታማነትን በተመለከተ በተደረገ ክትትልም፤ አገልግሎቱ የመንግስት የባንክ ሂሳብ መክፈትና መዝጋት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ስልጣን ሆኖ ሳለ ተቋሙ የራሱን የሂሳብ ቁጥር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግለሰቦች ስም ከፍቶ 17.9 ሚልዮን ብር ሰብስቧል፡፡
• የተቋሙ ሰራተኞች ከበር ጥበቃ ጀምሮ አስተባባሪዎችና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች ተገልጋዮችን የሚመቱ ፣ የሚገፈትሩእና አልባሌ ቃላቶችን የሚጠቀሙ መኖራቸውን በክዋኔ ኦዲት ተረጋግቷል ተብሏል፡፡
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር
• የከተሞች ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድና የሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ግንባታን በተመለከትተም በተደረገ ክትትል በ2015 በጀት ዓመት በ8 ከተሞች 67 መየህዝብና 95 የጋራ መፀዳጃ ቤቶች ባጠቃላይ 61 መፀዳጃ ቤቶችን እድሳት ለማከናወን ታቅዶ መፈፀም የተቻለው 25 መፀዳጃ ቤቶችወይም 15 ከመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡
ጤና ሚኒስቴር
• የፌደራል ሆስፒታሎች ቆሻሻሻ አያያዝ እና አዋጋገድን በተመለከተ በተደገ ክትትል፤ በአለርት አጠቃላይ ሆስፒታል የአመድም ሆነ የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ ቦታ በለመኖሩ ምክንያት ፕላሴንታ በግቢ ውስጥ በሚገኙ ዛፎች ውስጥ ዝቅተኛ ቦታ ላይ ለእንስሳትና ለዝናብ ክፍት በሆነ መልኩ ተከማችቶ መኖሩንና ከማቃጣያ የወጣው አመድ በ5 የተለያዩ ቦታዎች የተከማቸ መሆኑን የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያቤት ተናግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments