በኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና አገልግሎት በብዙ ችግሮች እንደሚፈተን ይነገራል፡፡
ከነዚህም መካከል፤ የህክምና መሳሪያዎችና ሌሎች የህክምና ግብዓቶች አለመኖር ተጠቃሽ ነው፡፡
በህክምና ግብዓት እጥረት ምክንያት፤ ህሙማን ተገቢውን ህክምና ሳያገኙ በረጅም ቀጠሮ ምክንያት ለሞት እየተዳረጉ ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች መካከል የ30 በመቶውን ድርሻ የሚይዘው የጡት ካንሰር እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የማህጸን በር ካንሰር በ13.4 በመቶ እና የትልቁ አንጀት ካንሰር ደግሞ 5.7 በመቶ በመያዝ ይከተላሉ፡፡
ከእነዚህ በተጨማሪ በተለያየ የካነሰር ዓይነቶች የተያዙ ሰዎች በመድሃኒት አለማግኘት፣ በባለሞያ እጥረት፣ በመሳሪያዎች ውስንነት እና በሌሎችም ምክንያቶች እጅጉን እየተቸገሩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments