top of page

ሰኔ 11 2017 - ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ታንዛንያ ለመሸጥ በዝግጅት ላይ መሆኗም ተነግሯል

  • Jun 18, 2025
  • 1 min read

የናይል ተፋሰስ ሀገራት በጥናትና መረጃ ላይ የተመሰረተ ልምድ የሚለዋወጡበት ቀጠናዊ ትብብር መፍጠርን ታሳቢ ያደረገው አራተኛው አፍሪራን ዞናዊ ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡


ቀጠናዊ ጉባኤውን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ባለቤት ሆኖ ያሰናዳው ሲሆን ቀጠናውን በኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማት ማስተሳሰር የጋራ ለሆነ ልማት ያለው ፋይዳ ላይ መምከር የዘንድሮ አራተኛ ጉባኤ ሀሳብ ሆኖ ተመርጧል።


በዝግጅቱ ላይ ተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከሰሃራ በስተደቡብ ባሉ ሀገራት ያለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አነስተኛ ሽፋን አንስተው በተለይ በአፍሪካ በከተማና ገጠር ያለው ሽፋን በጣም የተራራቅና ብዙ መስራትን የሚፈልግ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ ማሳደግን በተመለከተ ሲያነሱም ከፍጻሜው የደረሰው የህዳሴው ግድብን ጉዳይ አንስተዋል።


የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጠናው ሀገሮችም ሀብት ሆኖ መቆጠር ያለበት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡


የቀጠናው ሀገሮች በኤሌክትሪክ ኃይል ለማገናኘት በተሠራ ስራ ኢትዮጵያ ለሱዳን ኬንያና ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል በሽያጭ እንደምታቀርብ አንስተው ይሄንን በኤሌክትሪክ ቀጠናውን የማስተሳሰር ሰራን በማስፋት ለደቡብ ሱዳን ሶማሊያና ታንዛንያም ኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡


የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሃብታሙ ይተፋ በዓለም ዙሪያ ከ700 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ኤሌክትሪክ የማያገኝ መሆኑን በማንሳት ከዚህ ውስጥ ወደ 600 ሚሊየን የሚሆነው ህዝብ ከሰሃራ በስተደቡብ ያለ መሆኑን አንስተዋል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ

Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡

ሐምሌ 15 2018 በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት የህፃናት ማቆያዎቹ ጥቂት ነበሩ ያለው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን ላይ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተውበታል ብሏል፡፡ ጥናቱም በግል እና በመንግስት ማ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page