top of page

ሰኔ 11፣ 2016 - 73 መስሪያ ቤቶችና 15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የመንግስትን የግዢ አዋጅ እና መመሪያ ሳይከተሉ የ2.1 ቢሊየን ብር ግዢ ፈፅመዋል ተባለ

73 መስሪያ ቤቶችና 15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የመንግስትን የግዢ አዋጅ እና መመሪያ ሳይከተሉ የ2.1 ቢሊየን ብር ግዢ ፈፅመዋል ተባለ፡፡


ይህን ያለው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ነው፡፡


የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፌዴራል ዋና መስሪያ ቤት 2015 በጀት ዓመት የፋይናንስ ህጋዊነት ኦዲትና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ለፓርላማው አቅርቧል፡፡


መስሪያ ቤቶቹም በጨረታ መግዛት ሲገባቸው ያለ ጨረታ በቀጥታ የተፈፀመ ግዢ 1.8 ቢሊየን ብር፣ መስፈርቱን ሳያሟላ በውስን ጨረታ የተገዛ ብር 104.3 ሚሊዮን ብር፣ ግልፅ ጨረታ መውጣት ሲገባው በዋጋ ማወዳደሪያ የተፈፀመ ግዢ ብር 96.1 ሚሊየን እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሳይሰበሰብ የተፈፀመ ግዢ ብር 13.8 ሚሊየን ግዢ ተፈፅሟል ሲሉ የፌዴራል ዋና ኦዲተሯ መሰረት ዳምጤ ተናግረዋል፡፡


ከደንብና መመሪያ ውጪ ግዢ ከፈፀሙ መሰሪያ ቤቶች መካከል የገቢዎች ሚኒስቴር 1.4 ቢሊየን፣ የኢኖቬሽንና ዜግነት አገልግሎት 91 ሚሊዮን፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 65.5 ሚሊዮን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 62.9 ሚሊዮን ፣ ለኢትዮፕያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ 57.1 ሚሊዮን፣ ቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ 34 ሚሊየን ብር ከደንብና መመሪያ ውጪ ግዢ የፈፀሙ መሰሪያ ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


bottom of page