top of page

ሰኔ 11፣ 2016 - የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ቀላቅለው ይዘው የተገኙና ሌሎችም ህገወጥ ድርጊቶች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ተቋማት እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ

በአዲስ አበባ ከሚገኙ መድኃኒት መደብሮች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ቀላቅለው ይዘው የተገኙና ሌሎችም ህገወጥ ድርጊቶች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ተቋማት እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ፡፡


በተቋማቱ ላይ የተለያየ ደረጃ ቅጣት መጣሉን የተናገረው የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ነው፡፡


በ2016 በጀት ዓመት ባለስልጣን መ/ቤቱ ቁጥጥር ካደረገባቸው የመድኃኒት መደብሮች 19 የሚሆኑት በተገኘባቸው ችግር ቅጣት እንደተጣለባቸው ተነግሯል፡፡


የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ስራ አስኪያጇ ሙሉእመቤት ታደሰ ለሸገር እንደተናገሩት በከተማዋ የሚገኙ የመድኃኒት መደብሮችን መቆጣጠር የ/ቤቱ ኃላፊነት መሆኑንና እስካሁንም የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድኃኒቶችን ቀላቅለው በያዙ እና በሌሎችም ህገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ የተገኙ ተቋማት ተቀጥተዋል ብለዋል፡፡


ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች ሲገኙ የማስወገዱ ስራ የሚከውኑ ተቋማት መኖራቸውንና በአግባቡ ስለመወገዱም የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ማረጋገጫ ይሰጣል ተብሏል፡፡


በህክምና ተቋማትም ይሁን በመደብሮች የተበላሸ ወይም የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት መድኃኒት ማከማቸት የሚቻለው ቢበዛ ለ 6 ወራት ብቻ መሆኑ በመመሪያ ተደንግጓል፡፡


ምህረት ስዩም



コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page