16 የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፤ በመስሪያ ቤቱ ለሌሉና ከስራ ለተሰናበቱ ሰራተኞች ደመወዝ ሲከፍሉ ተገኝተዋል ተባለ፡፡
እነዚህ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለሌሉና ከስራ ለተሰናበቱ ሰራተኞች ብር 485,183.59 ብር ያላግባብ ከፍለው መገኘታቸው ተረጋግጧል፡፡
ይህንን ባደረኩት የኦዲት ሪፖርት አረጋግጫለሁ ያለው የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ነው፡፡

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ክፍያዎች መመሪያን ተከትለው እንዲፈፀሙ ተገቢው ክትትል ሊደረግ እንደሚገባ ተናግሯል፡፡
ያለአግባብ የተፈጸሙ ክፍያዎችም ተመላሽ መደረግ እንዳለበት በላክሁት ሪፖርት አሳስቤለሁ ብሏል፡፡
Comments