top of page

ሰኔ 10 2017 - የኢራኗ ርዕሰ ከተማ ቴሕራን በከባድ ፍንዳታ እየተናወጠች ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jun 17
  • 1 min read

የኢራኗ ርዕሰ ከተማ ቴሕራን በከባድ ፍንዳታ እየተናወጠች ነው ተባለ፡፡


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም የቴህራን ነዋሪዎች እያንዳንዳቸው መዲናዋን ለቅቀው እንዲወጡ ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ትራምፕ የአሜሪካንን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት አጣዳፊ ስብሰባ መጥራታቸውም ታውቋል፡፡


ፕሬዘዳንቱ የቡድን 7 አባል ሀገሮች ስብሰባቸውንም አሳጥረውታል ተብሏል፡፡


እስራኤል ትናንት በቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ የኢራንን መንግስታዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ መትታዋለች፡፡

የሕንፃ ፍርስራሽም ሲወድቅ በዚያው አጋጣሚ ታይቷል ተብሏል፡፡


እስራኤል በ #ኢራን የሚገኙ የሚሳየል ማስወንጨፊያ ስፍራዎችንም መደብደቧ ተሰምቷል፡፡


ኢራንም ወደ እስራኤል ሐይፋ ቴል አቪቭ እና ኢየሩሳሌም በርካታ ሚሳየሎችን መተኮሷ ታውቋል፡፡


አልጀዚራ እንደፃፈው ኢራን በ #እስራኤል ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ዓይነት ጥቃት እንደምትፈፅም ዝታለች፡፡


እስራኤል ካለፈው ዓርብ አንስቶ በኢራን ላይ በምትፈፅመው ድብደባ የተገደሉ ሰዎች ብዛት 224 ደርሷል፡፡


በእስራኤልም 24 ሰዎች መገደላቸው የሀገሪቱ ሹሞች ተናግረዋል፡፡


የኔነህ ሲሳይ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page