top of page

ሰኔ 10፣ 2016 - ''ያለ ንግድ ፍቃድ የሚሰሩ፣ ባዕድ ነገሮችን ከምግብ ጋር ቀላቅለው የሚሸጡ ነጋዴዎችን አልታገስም'' የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከዚህ በኋላ ያለ ንግድ ፍቃድ የሚሰሩትንም ይሁን ባዕድ ነገሮችን ከምግብ ጋር ቀላቅለው የሚሸጡ ነጋዴዎችን አልታገስም አለ፡፡


በአዲስ አበባ ምንም ዓይነት የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው፤ በየመንደሩ ባለ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩትን ለመቆጣጠር መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡


መመሪያው ‘’የመንደር ንግድ ቁጥጥር የአሰራር ሥርዓት’’ በሚል የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ ሰይሞታል፡፡


በየመንደሩ ያሉ ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚሰሩትን፤ ጥራታቸውን ያልጠበቁና የመጠቀሚ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ምርቶች የሚሸጡ፤ ባዕድ ነገሮችን ከምግብ ጋር ቀላቅለው የሚሸጡ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡


በከተማዋ 400 ሺህ የንግድ ድርጅቶች ፍቃድ አውጥተው እየሰሩ ቢሆንም እዚህም እዚያም፣ በየጥጋ ጥጉ የሚሰሩ ፍቃድ የሌላቸው ነጋዴዎችም ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡



Comments


bottom of page