በርካታ ክልሎች ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ በሆኑ ምክንያቶች ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች በራሳቸው ዕርዳታ ማቅረብ ጀምረዋል ተባለ።
የፌዴራል መንግስትን ድጋፍ አሁንም እየፈለጉ ያሉት ብዙ ተረጂዎች ያሉባቸው እና ቅፅበታዊ አደጋ የሚደጋግማቸው ክልሎች እንደሆኑ ሠምተናል።
ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ በሆኑ ምክንያቶች ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች ክልሎች በራሳቸው ዕርዳታ የማቅረብ አቅም እንዲፈጥሩ በተለያየ ጊዜ ውይይት ተካሂዶ ከመግባባት መደረሱን፤ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ አታለለ አቦሃይ ነግረውናል።
በዚሁ መሰረትም አሁን ላይ በርከት ያሉ ክልሎች ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች በራሳቸው ዕርዳታ እያቀረቡ ይገኛሉ ብለዋል።
አሁንም የፌዴራል መንግስትን ዕገዛ እየጠየቁ ያሉት ብዙ ድጋፍ ፈላጊዎች ያሉባቸው እና እንደ ትግራይ እና አማራ ያሉ ክልሎች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
ቅጽበታዊ የሆኑ ተፈጥሯዊ አደጋዎች የሚደጋገሙባቸው እንደ አፋር እና ሶማሌ ያሉ ክልሎችም ድጋፍ ፈላጊዎችን ለመርዳት የፌዴራል መንግስትን ዕገዛ እንደሚፈልጉ ሠምተናል።
Comments