top of page

ምጣኔ ሐብት - ሀገሮች የማክሮ ኢኮኖሚያቸው ሲረበሽ ምን ያደርጋሉ?

  • sheger1021fm
  • Jul 1
  • 1 min read

ሰኔ 24 2017


ሀገሮች የማክሮ ኢኮኖሚያቸው ሲታመም ወይም ሲንጋደድ ወይም አጠቃላይ ብሔራዊ ምጣኔ ሐብታቸው ሲረበሽ ምን ያደርጋሉ?


ለዘመናት የሚጓዙበትን መንገድ በመፈተሽ ቀድመው ከሚተገብሩት ጠንካራ የማክሮ ኢኮኖሚ መሳሪያ አንደኛው እና ዋነኛው የብር ወይም የገንዘባቸውን ዋጋ በማዳከም በገበያው እንዲወሰን ማድረግ ነው።


ይህ ሀሳብ ወይም መሳሪያ በሀገሮቹ ብሔራዊ ጉዳዮች ብቻ የሚወሰን አይደለም።


እንደውም የምዕራባውያኖቹ ጫናም አለበት ተብሎ ይተቻል፤ በእርግጥ ይህ ሀሳብ እራሱ በባለሞያዎቹ ለሁለት ይከፈላል።


የሚስማሙበትም አሉ የማይስማሙበትም ባለሞያዎች ሀሳብ ይሰማል።


የሆነው ሆኖ ለምሳሌ ሱዳን እና ናይጄሪያ ይህ በመተግበራቸው ምክንያት ገንዘባቸው በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁሎ ሳይሳኩላቸው ከቀሩት ሀገሮች ምድብ ገብተዋል።


ኢትዮጵያም ይህንኑ ተመሳሳይ እርምጃ የወሰደችው አምና ነው።


በዚህ ተመሳሳይ እርምጃ ኢትዮጵያ ተሳክቶላታል ወይስ አልተሳካላትም ተብሎ ይጠየቃል። አዎን ተሳክቷል ከተባለስ እንዴት?


በገንዘብ ቁጥጥር፣ በውጭ ምንዛሪ አስተዳደር እና በሌሎች የምጣኔ ሐብት መንገዶች አመላካቾቹ ምንድናቸው? አይ አልተሳካም ገና ይቀራል ከተባለስ መሞገቻው ሀሳብ ምን ሊሆን ይችላል?


ማክሮ ኢኮኖሚው ፍፁም የተረጋጋ ነው ከተባለስ ሰላምና ነፃነቱስ የታለ፣ ኢንቨስትመንቱስ ለምን ደከመ? የህዝቡስ ኑሮ ለምን አልተቀየረም ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ እንዴት ማስረዳት ይችላል?


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…….


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page