top of page

ምርትና አገልግሎት ያላቸውን፣ ሸማቹንና አሻሻጭን የሚያገናኝ የሞባይል መተግበሪያ በይፉ ስራ መጀመሩ ተነገረ።

  • sheger1021fm
  • Dec 27, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 18/2018

 

ምርትና አገልግሎት ያላቸውን፣ ሸማቹንና አሻሻጭን የሚያገናኝ የሞባይል መተግበሪያ በይፉ ስራ መጀመሩ ተነገረ።

 

መተግበሪያው "ዳንቴል" ይባላል።

 

በዳንቴል ሶፍትዌር የተዘጋጀው "ዳንቴል" የሞባይል መተግበሪያ አምራቾች ምርታቸውን፣ አገልገሎት አቅራቢዎች ያላቸውን አገልግሎት ሙሉ መረጃ የሚያስቀምጡበት፣ መረጃውን ደግሞ በየራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚያጋሩና ሽያጭ እንዲከናወን የሚያደረጉ ደግሞ የኮሚሽን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችል ስርዓት ይዞ የመጣ ነው።

 

ይህም ለሸማቹ ገበያ ወጥቼ የት ምን አገኛለሁ የሚለውን የሚያቀልል፣ ለአምራቹም ሰፊ የገበያ እድል የሚፈጥር፣ በተለይ በሽያጭ ስራ ገቢ ለማግኘት ለሚፈልጉ ስልካቸውን ተጠቅመው ገቢ እንዲያገኙ የሚያስች እንደሆነ የድርጅቱ ሀላፊዎች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

 

መተግበሪያው በሰው ሰራሽ አስተውህሎት(AI) ታግዞ ተጠቃሚዎችን ያማክራል ተብሏል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ፍቅሩ አምባቸው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page