ሚያዝያ 9 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ከአማዞን፣ ከማይክሮሶፍት እና ከኦራክል የክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች ባነሰ ዋጋ የገነባሁትን ክላውድ ለሚፈልጉት ሽያጭ ማድረጉን ተናግሯል
- sheger1021fm
- Apr 17
- 1 min read
ኢትዮ ቴሌኮም ከአማዞን፣ ከማይክሮሶፍት እና ከኦራክል የክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች ባነሰ ዋጋ የገነባሁትን ክላውድ ለሚፈልጉት ሽያጭ ማድረጉን ተናግሯል።
እሳካሁንም ከ350 በላይ ድርጀቶች አገልግሎቱን አግኝተዋል ተብሏል።
ለመንግስት አገልግሎት ሰጭዎች፣ ለመገናኛ ብዙሀን፣ ለማይክሮ ፋይናንስ እና ለባንኮች የክላውድ አገልግሎቱን በስፋት ማቅረቡን ሰምተናል።
ኩባንያው እስካሁን ከ300 በላይ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን ሽጫለሁ ያለ ሲሆን የገዢ ችግር የለብኝም ብሏል።
ኩባንያው 3ኛውንም ክላውድ እየገነባ መሆኑ ሰምተናል።
በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ የኢንፎርሜሽን ኦፊሰር አቶ እንዳለ አስራት ኩባንያው በመጀመርያው እና ሁለተኛው ምእራፍ የገነባው የክላውድ አገልግሎት ሸጦ ጨርሶ ሶስተኛውን ለመገንባት ወደ ኢንቨስትመንት ገብቷል ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የክላውድ አገልግሎቱን የጀመርኩት አገልግሎት ፈላጊዎች ለሰርቨር የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ እና ተያይዞ የሚመጣውን ድካም ለማስቀረት መሆኑን ተናግሯል።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comentarios