top of page

ሚያዝያ 9፣2016 - የሚኒስትሮች ም/ቤት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን አጸደቀ

  • sheger1021fm
  • Apr 17, 2024
  • 1 min read

በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸውን ም/ቤቱ አስታውሷል፡፡


ሆኖም እነዚህ አሰራሮች በእውነት፣ በዕርቅ፣ በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም ብሏል።


ስለሆነም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡


ምክር ቤቱም በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ተናግሯል፡፡


የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከዚህ በተጨማሪም የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደርን ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት፤ እንዲሁም ከጊዜው ጋር የሚራመድ የአስራር ስርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተወያይቶ ለህዝብ አንደራሴዎች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page