top of page

ሚያዝያ 8 2017 - ለየንሳኔ በዓል ከ6,500 በላይ የቁም እንሰሳት እርድ ለመከወን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Apr 16
  • 1 min read

ለመጪው የትንሳኔ በዓል ከ6,500 በላይ የቁም እንሰሳት እርድ ለመከወን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ተናገረ።


ድርጅቱ የፊታችን እሁድ ለሚከበረው የትንሳኤ በዓል ለማህበረሰቡ የእንሰሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን  ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።


በዚህም ወቅት የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ አታክልቲ ገብረ ሚካኤል ለበዓሉ ከ4,000 በላይ በሬና ከ2,500 በላይ በግና ፍየል በድምሩ ከ6,500 በላይ የእንሰሳት እርድ ለመከወን ተዘጋጅተናል ብለዋል።

ድርጅቱ በዋናው ቄራና አቃቂ ባለው ቅርንጫፉ የእርድ አገልግሎቱን ፈልገው ለሚመጡ ደምበኞቹ አንዱን በሬ በ1,470 ብር እንዲሁም አንዱን በግና ፍየል በ130 ብር እንደሚያርድ አቶ አታክልቲ ጠቅሰዋል።


የሚፈለገውን ያህል አገልግሎት ለመስጠት ካሉት1ሺህ41 ቋሚ ሰራተኞቹ በተጨማሪ 260 ጊዜያዊ ሰራተኞች ቅጥር በመከወን ስልጠና መስጠቱንም ጠቁመዋል።


እርድ የሚከወንባቸውን ቦታዎችና የእንሰሳቱ ማቆያ በረት የማስፋፊያ ስራ ተሰርቷል ያሉት ሃላፊው ለበዓሉ የሚታረደውን የሚያከፋፍሉ ከ40 በላይ የስጋ ማጓጓዛ ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውንም አስረድተዋል።


የቄራዎች ድርጅት ይህንን መሰል ዝግጅት ባደርግም  ማህበረሰቡ በቄዎች  የማሳረድ ልማድ ስለሌለው ከአቅሜ በታች እየሰራሁ ነው ማለቱንም ሰምተናል።


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page