top of page

ሚያዝያ 8 2017 - ለትንሣኤ በዓል ዘይትና ስኳር በሶስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች አማካይነት እየተሰራጨ እንደሚገኝ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚ/ር ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Apr 16
  • 1 min read

ለትንሣኤ በዓል ከ9.5 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይትና 200,000 ኩንታል ስኳር በሶስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች አማካይነት ለህብረተሰቡ እየተሰራጨ እንደሚገኝ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናገረ።


በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ ነዋሪዎች ምርቶቹን በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ይችላሉም ብሏል።


ለትንሳኤ በዓል ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይትና 200 ሺህ ኩንታል ስኳር መንግስት በድጎማ ለህብረተሰቡ እንደቀረበ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመልክቷል።


ምርቶቹ እየተሰራጩ ያሉት በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ፤ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት እና፤

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አማካይነት እንደሆነ የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ነግረውናል።


በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ ነዋሪዎች ምርቶቹን በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።


ምርቶቹ በመንግስት ድጎማ የተደረገባቸው ስለሆኑ መሸጫቸው አነስተኛ ነው የሚሉት አቶ ወንድሙ ይኸው ዋጋቸው እንደሚለጠፍባቸውም ተናግረዋል።


በመንግስት ድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች ባሻገር 1438 የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎችም ለበዓሉ የሚሆኑ ፤ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶችን እየሸጡ እንደሚገኙ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።


ለበዓሉ የሚሆኑ የፍጆታ ምርቶችን ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ከማድረግ ጎን ለጎን ሆን ተብሎ በሚፈጠር እጥረት ዋጋ እንዳይጨምር፤ ከክልሎች ጋር በመሆን ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም አቶ ወንድሙ ተናግረዋል።


ይህንኑ ስራ የሚሰራ ግብረ ሃይል በሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳድሮች መዋቀሩን አክለዋል።


ህብረተሰቡም በግብይት ወቅት የሚፈጸም ህገ ወጥ ተግባር ከገጠመው በአቅራቢያው ላሉ የፀጥታ አካላት እና ለዚሁ ግብረ ሃይል ጥቆማ እንዲሰጥ አቶ ወንድሙ ጠይቀዋል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page