top of page

ሚያዝያ 7 2017 - ጦርነትና ግጭቶች የስራ አጥ ቁጥርን እንዲጨምር እያደረገው መሆኑን ጥናት አሳየ፡፡

  • sheger1021fm
  • Apr 15
  • 1 min read

ጦርነትና ግጭቶች የስራ አጥ ቁጥርን እንዲጨምር እያደረገው መሆኑን ጥናት አሳየ፡፡


የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በበኩሉ እኔ የማውቀው ሰፊ የስራ እድል እየተፈጠረ መሆኑን ነው ብሏል፡፡


ጥናቱን ያጠናው ያንግ ላይቨስ የተሰኘ ተቋም ሲሆን ጥናቱም በወጣቶችና በቤተሰብ ሥር የሚገኙ ልጆች ላይ መሰረት ያደረገ እንደሆነ ሰምተናል፡፡


በዚህም የጥናቱ ግኝት 22 ዓመት የሞላቸው ወጣት ልጆች በትምህርት አሊያም ደግሞ በስራ ላይ መሆን ሲገባቸው ከሁለቱም ሳይሆኑ መቅረታቸውን አጥኚዎቹ ነግረውናል፡፡


የስራ አጥ ቁጥሩ መጨመሩ የታየው በትግራይና በአማራ ክልል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡


ይህ ደግሞ በክልሎቹ ያለው ግጭት ያመጣው ጫና እንደሆነና ለእነዚህ ወጣቶች በመንግስት በኩል የስራ እድል እንዳልተፈጠረላቸው አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡


ተቋሙ ከዚህ ቀደም ካደረጉት ጥናት ጋር ሲነፃፀር የስራ አጥ ቁጥሩ በአሁኑ ጨምሯል ሲሉ የነገሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የዚህ ጥናት አካል ሆኖ የተሳተፉት ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሃና ናቸው፡፡


የስራ ክህሎት ሚኒስቴር በበኩሉ ጥናቱ የስራ አጥ ቁጥር ጨምሯል ቢልም በእኔ በኩል ሰፊ የሆነ የስራ እድል ለወጣቶች ተፈጥሯል ብሏል፡፡


የስራ አጥ ወጣቶች የሚመዘገቡበት ስርዓት ተዘርግቶ በአስር ወራት ውስጥ የሰለጠነ የሰው ኃይል በመፍጠር ከ341,000 በላይ የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት መደረጉን የነገሩን በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የህግ ዝግጅትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳዊት ላቀው ናቸው፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….




ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page