ሚያዝያ 7 2017 - ባለፉት 9 ወራት ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ከትራፊክ ቅጣት መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣናት ተናገረ።
- sheger1021fm
- Apr 15
- 1 min read
ባለፉት 9 ወራት ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ከትራፊክ ቅጣት መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣናት ተናገረ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ባለፉት 9 ወራት ከትራፊክ እና ከመሰል ቅጣቶች በአጠቃላይ ከ700ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግሯል።
በከተማዋ ከሚስተዋለው የትራፊክ ደንብ ጥሰት ውስጥ 40 በመቶው የፍጥነት ወሰን ህግን አለማክበር ነው ተብሏል።

የትራፊክ ቁጥጥሩን ለማዘመን፣ የሙስና ተጋላጭነትን እና የደንብ ጥሰትን ለመቀነስ፣ የተገልጋዮችን እንግልት ለማስቀረት እንዲሁም መሰል የአሰራር ስርአትን ለማሻሻል ዲጂታል አሰራርን እየተገበርኩ ነው ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ ተናግሯል።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚዴቅሳ በትራፊክ ደንብ እና በመሰል ጥሰቶች ቅጣት የምንጥለው ገቢ ለመሰብሰብ ሳይሆን ህግን ለማስከበር ነው ብለዋል።
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments