ሚያዝያ 7 2017 - በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ ፈቃድ ወስደው እየሰሩ ያሉ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቁጥር 51 መድረሱን ሰምተናል
- sheger1021fm
- Apr 15
- 1 min read
ማስጠንቀቂያ ሰጥቻቸው የነበሩ ሁሉም የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አሁን ላይ መስፈርቱን ስላሟሉ፤ የህጋዊነት ወረቀት ሰጥቻቸዋለሁ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለልጣን ተናገረ፡፡
ባለስልጣኑ ከወራት በፊት ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሀገሪቱ በስርጭት ላይ ያሉ #የሀይማኖት_የቴሌቪዥን_ጣቢያዎች እንዳሉ ጠቅሶ፤ እነዚህ ተቋማት አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን አሟልተው ካልተመዘገቡ ህጋዊ ርምጃ እውስዳለሁ በማለት ማስጠንቀቁ የሚታወስ ነው፡፡
በወቅቱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው የሀይማት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፤
1. ኦሲኤን (OCN TV)
2. ሐሪማ ቴሌቪዥን (Harima TV)
3. ፕረዘንስ ቴሌቪዥን (Presence TV) እና
4. ጀሰስ ወንደርፉል ቴሌቪዥን (Jesus Wonderful TV) ነበሩ፡፡
እነዚህ የሀይማት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በባለስልጣኑ መመዝገባቸውን ተከትሎ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ የሚተላለፍ ፍቃድ ያልተሰጠው ምንም የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሌለ የነገሩን፤ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለልጣን የመገናኛ ብዙሀን ፈቃድ ምዝገባና እውቅና ዴስክ ሀላፊ ደሴ ከፋለ ናቸው፡፡

የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲባልም፤ ተቋማቱ ሀይማኖታዊ አስተምህሮቶቻቸውን ለምዕመኑ ለማድረስ የሚጠቀሟቸው እንጂ ለትርፍ ወይም ለ #ንግድ ተብለው የሚቋቋሙ አይደሉም ሲሉም ተናግረዋል አቶ ደሴ፡፡
ለመሆኑ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤት መሆን የሚችለው ማነው ያልናቸው አቶ ደሴ፤ በአዋጅ የተቋቋመ የሀይማኖት ተቋም፣ በተቋማቱ ውስጥ እውቅና ያላቸው የተለያዩ ማህበራት ባለቤት መሆን ይችላሉ ብለዋል፡፡
የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለምዝገባ ሲመጡ፤ በአዋጅ ከተቋቋሙ ተቋማት ከሆኑ የተቋቋሙበት አዋጅ፣ ማህበራት ከሆኑ ደግሞ ከታቀፉበትና እውቅና ካለው ተቋም እንዲሁም ከሰላም ሚኒስቴር የተሰጣቸውን ሰርተፊኬት ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ኤዲቶሪያል ፖሊሲ፣ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል እና መሰል ዶክሜንቶች እንደሚጠየቁም ሀላፊው ነግረውናል፡፡
በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ ፈቃድ ወስደው እየሰሩ ያሉ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቁጥር 51 መድረሱንም ከባለስልጣኑ ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments