ሚያዝያ 6 2017 - የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲጂታል ሎተሪ ጀመረ።
- sheger1021fm
- Apr 14
- 1 min read
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲጂታል ሎተሪ ጀመረ።
የተጀመረው የዲጂታል ሎተሪ በሁለት መንገድ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
አንደኛው የቁጥር ሎተሪዎችን በመጀመርያ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በከፊል ዲጅታል ማድረግ ነው ተብሏል፡፡

ይህም ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ ጎን ለጎን በዲጅታል፣ በ ሞባይል መተግበሪያዎች አማካኝነት ቀርቧል።
ከዚህ በተጨማሪም የሚፋቁ የፈጣንና ቢንጎ ሎተሪዎችን በዲጅታል መጥተዋል ሲባል ሰምተናል፡፡
ይህን የዲጂታል ሎተሪ ''ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ'' ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በጋራ መሰራቱ ተነግሯል።
የዲጂታል ሎተሪው በእጅ ስልክ፣ በኮምፒውተር፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፣ በዩስስዲ፣ ስካን አድርጎ በመጫዎት፣ ስልክ ደዉሎ በመጫወት፣ ከእድል አዟሪዎች በፖስ ማሽን በመግዛት እድልን መሞከር ይቻላል ተብሏል።
የዛሬ 64 ዓመት 50,000 ብር እጣ ያወጣውና ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዛሬ ላይ የ50 ሚሊዮን ብር እጣ ገበያ ላይ አውሏል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments