ሚያዝያ 6 2017 - አዋሽ ባንክ ለ10 ሺህ እጅ ላጠራቸው ሰዎች የሚያደርገውን የበዓል መዋያ ድጋፍ ጀመረ
- sheger1021fm
- Apr 14
- 1 min read
አዋሽ ባንክ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ10 ሺህ እጅ ላጠራቸው ሰዎች የሚያደርገውን የበዓል መዋያ ድጋፍ በዛሬው እለት ጀመረ።
ኩባንያው ለዚህ ሲልም 63 ሚሊዮን ብር መመደቡን ተናግሯል።

በዛሬው እለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በተካሄደ የድጋፍ ስነ ስርዓት 250 አቅመ ደካማ ሰዎች ዱቄትና ዘይት እንዲሁም ለዶሮና ሽንኩርት መግዣ ጥሬ ገንዘብ ተሰጥቷቸዋል።
ዝግጅቱ ላይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተወካዮች፣ የቅድስት ስላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ እንዲሁም የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራሁ ተገኝተዋል።
አዋሽ ባንክ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሃገሪቱ በሚገኙ ከአንድ መቶ በላይ የድጋፍ መስጫ ጣቢያዎች ከአስር ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ ጧሪ ለሌላቸው አረጋዊያን እና ሌሎች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል።
ኩባንያው በተለያዩ ጊዜያት በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ኦያደረገ መሆንኑን ተጠቅሷል።
ባንኩ በቅርቡ የ1446ኛዉን የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ከተሞች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ለሙስሊም ወገኖች ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ አስታውሷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments