ሚያዝያ 6 2017 - በየቦታው ገመድ ተወጥሮ የሚጠየቅ የኬላ ክፍያ
- sheger1021fm
- Apr 14
- 1 min read
በየቦታው ገመድ ተወጥሮ የሚጠየቅ የ #ኬላ_ክፍያ ህገ ወጥ ነው መቆምም አለበት፤ ሲል መንግስት በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡
ይህን ማድረግ ግን አልተቻለም ተብሏል፡፡
የከባድ ተሽከርካሪ ማህበራት አሽከርካሪዎች በየከተማው በየተወሰነ ኪሎ ሜትሩ ልዩነት ባሉ ኬላዎች በሺዎች የሚቆጠር ብር እንጠየቃለን ብለዋል፡፡
ችግሩ ለሸቀጦች ዋጋ መናር ምክንያት መሆኑም በፓርላማ ጭምር ሲነገር የቆየ ጉዳይ ነው፡፡
በኦሮሚያና በአማራ ክልል አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች በየመንገዱ ባሉ የኬላ ክፍያዎች በብርቱ እየተፈተንን ነው ብለዋል፡፡
እነዚህ ህገ ወጥ ክፍያዎችን መንግስት ካስቀመጠው ተመን በላይ እንዲከፍሉ እንደተደረገም አሽከርካሪዎች አስረድቷል፡፡
በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት እና ሶስት ቦታዎች ላይ እንደሚከፍሉም ከአሽከርካሪዎች ሰምተናል፡፡
አላግባብ የሆነ ክፍያ ለምን እንጠየቃለን በምንልበት ወቅት እስከመደብደብ እንደርሳለን ሲሉ ቅሬታቸው ለሸገር ራዲዮ ያቀረቡ አሽከርካሪዎች ይናገራሉ::
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments